1/2
የአማኑኤል ቤተክርስቲያን በባፎሎ እና በአካባቢው በሚኖሩ ጥቂት አማኞች መሰባሰብ ምክንያት እንደ ኤ.አ. በ2012 ተመሠረትች። “አማኑኤል” በሚል ስያሜ ከመደራጀቷ በፊት በአካባቢው የነበሩ ቅዱሳን በየቤታችው በመገናኘት ሲፀልዩ፤በእርስ በእርሳቸው ሲመካከሩ እንዲሁም ከተለያየ አገር በሚመጡ አገልጋዮች እየተገለገሉ ቆይተዋል። ሆኖም ሀብረቱ የቤተክርስቲያን ቅርፅ ይዞ የተደራጀው እና መጠሪያም ስያሜ ያገኘው ከላይ በተጠቀሰው ዓመት ነበረ። እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያኗ ከገለፀው ታላቅ ፍቅሩ እና ምህረቱ የተነሳ ባለፉት ፡ ጥቂት አመታት ፡ ጸንታ በመቆም ተልኮዋን እየተወጣች ትገኛለች። ቤተክርስቲያኗ ፡በባፍሎ ከተማ እና አካባቢው የሚኖሩ፡ የኢትዮጵያውያን እና የኤርትራውያን አማኞች፡ ህብረት ናት።
Buffalo Amanuel Church started in 2012 with small group of believers in the city of Buffalo.Due to the exceedingly abundant Grace of the Lord, with the Faith and Love which is in Christ Jesus; the Church is able to stand firm and continue the divine mission.The congregation is comprised of believers from Ethiopia and Eritrea with the vision of reaching the community in the Greater Buffalo Area with the Gospel of Jesus Christ.
መደበኛ የእሁድ አምልኮ መሰብሰባችን ቀጥሏል።
በኮቪድ-19 ምክንያት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እና የፀሎት አገልግሎት ዘርፎች በዙም ይካሄዳሉ።