የቤተክርስቲያኗ የአመራር እና የአስተዳደር መሠረቱ የምዕመናን ጉባኤ ነው። በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት የቤተክርስቲያኗ ዋና መጋቢ ከጠቅላላው ጉባኤ ጋር በመሆን ሽማግሌዎችን በመምረጥ እና በማስመረጥ የአመራር ክፍሉን ያጠናክራሉ። መንፈሳዊ ዘርፉ በመጋቢው እና በመንፈሳዊ አገልጋዮች ይካሄዳል። የአስተዳደር ዘርፉ በተመረጡ ሽማግሌዎች፣ ዲያቆናት እና በቢሮ ሠራተኞች ይተዳደራል።
በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
የሐዋ ሥራ: 20 ፥ 28
በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤ የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ።
1ኛ የጴጥሮስ: 5 ፤ 2 - 4
መጋቢ ፋሲል ጌታቸው ታፈሰ
Paster Fasil G. Tafesse
Say something interesting about your business here.
1 ቆሮንቶስ 14:26 'ወንድሞች ሆይ፤ እንግዲህ ምን እንበል? በምትሰበሰቡበት ጊዜ እያንዳንዱ መዝሙር አለው፤ ትምህርት አለው፤ መግለጥ አለው፤ በልሳን መናገር አለው፤ መተርጐም አለው። ይህ ሁሉ ግን ለማነጽ ይሁን። '
1CO.14.26 "What then shall we say, brothers and sisters? When you come together, each of you has a hymn, or a word of instruction, a revelation, a tongue or an interpretation. Everything must be done so that the church may be built up.
'ኢየሱስ ግን ሕፃናቱን ወደ ራሱ ጠርቶ እንዲህ አለ፤ “ሕፃናት ወደ እኔ እንዲመጡ ፍቀዱላቸው፤ አትከልክሏቸው፤ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ እነዚህ ላሉት ናትና። '
ሉቃስ 18:16
Dut 6:7 "mpress them on your children. Talk about them when you sit at home and when you walk along the road, when you lie down and when you get up.
ዘዳግም 6:7 'ለልጆችህም አስጠናቸው፤ በቤትህ ስትቀመጥ፣ በመንገድም ስትሄድ፣ ስትተኛና ስትነሣም ስለ እነርሱ ተናገር። '
'በዚህ ጊዜ ሴቶች ከሩቅ ሆነው ይመለከቱ ነበር፤ ከእነርሱም መካከል መግደላዊት ማርያም፣ የታናሹ ያዕቆብና የዮሳ እናት ማርያም፣ እንዲሁም ሰሎሜ ነበሩ፤ እነዚህ ሴቶች በገሊላ ሲከተሉትና ሲያገለግሉት የነበሩ ናቸው፤ ደግሞም አብረውት ወደ ኢየሩሳሌም የመጡ ሌሎች ብዙ ሴቶች ነበሩ። '
ማርቆስ 15:40-41/MRK.15.40-41
'እንግዲህ ከሁሉ አስቀድሞ ልመናና ጸሎት፣ ምልጃና ምስጋና ለሰዎች ሁሉ፣ ለነገሥታትና ለባለሥልጣናት ሁሉ እንዲደረግ አሳስባለሁ፤ '
1 ጢሞቴዎስ 2:1/1TI.2.1
መደበኛ የእሁድ አምልኮ መሰብሰባችን ቀጥሏል።
በኮቪድ-19 ምክንያት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እና የፀሎት አገልግሎት ዘርፎች በዙም ይካሄዳሉ።